The Barter & Skill Exchange Network

Group Feed

Show by
  • Groups

    የዲጅታል ሂሳብ አያያዝ እና ታክስ አማካሪነት አገልግሎት የምንሰጥ ድርጅት ነን። አዳዲስ የቴክኖሎጂ ምርቶቻችንን ለማስተዋወቅ ትልቅ የህዝብ ግንኙነት ፕሮግራም (Event) ማዘጋጀት እንፈልጋለን። ዝግጅቱንም በሙያዊ ደረጃ የሚያስተባብርልን ድርጅት እንፈልጋለን፤ ክፍያውን በቀጥታ በገንዘብ ፋንታ ለድርጅቱ ሰራተኞች የሚሆን የዓመት ሙሉ የሂሳብ አያያዝ እና የታክስ ማስታወቂያ ዝግጅት አገልግሎት በቅይይር እናቀርባለን። በ inbox እንወያይ።

    • Groups

      በቢዝነስ አማካሪነት እና በሂሳብ አያያዝ ስራዎች ላይ የተሰማራን ድርጅት ነን። አዲሱንና ሰፊውን ቢሯችንን በቋሚነት የሚያጸዳ እና የጥገና አገልግሎት የሚሰጠን አስተማማኝ የጽዳት ድርጅት እንፈልጋለን። ከ 35-45% የሚሆነውን ክፍያ መክፈል የምንፈልገው እኛ በምንሰጠው የታክስ ማስታወቂያ ዝግጅት እና የህግ ማማከር አገልግሎት በቅይይር (Barter) መልክ ነው። በውስጥ መስመር አናግሩን።

      • Groups

        የድርጅታችንን የትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች መለዋወጫ ዕቃ መግዛት እና የጥገና አገልግሎት ማግኘት እንፈልጋለን። ሙሉ ክፍያውን በቀጥታ በገንዘብ በመክፈል ፋንታ ከ 5-15 % የሚሆነውን ለጋራዡ ባለቤቶች የሚሆን የሂሳብ አያያዝ፣ የታክስ ማስታወቂያ ዝግጅት ወይም የህግ አማካሪ አገልግሎት በቅይይር እናቀርባለን። አብሮ መስራት የሚፈልግ መኪና ጥገና ቤት በውስጥ መስመር ያግኙን።

        • Groups

          በሶሻል ሚዲያ ማርኬቲንግ እና በብራንዲንግ ስራዎች ላይ የበርካታ ዓመታት ልምድ ያለው ድርጅት ነን። አሁን ላይ ለሰራተኞቻችን ዓመታዊ የጤና ምርመራ (Medical Checkup) እና የህክምና አገልግሎት የሚሰጠን ጥራት ያለው ክሊኒክ እንፈልጋለን። እኛ ከምናደርግላቸው የዲጂታል ማስታወቂያ እና የደንበኛ ማስፋፊያ ስራ ጋር ተመጣጣኝ በሆነ መልኩ በቅይይር እንሰራለን። በ inbox እንነጋገር ።

          • Groups

            የእኛ የዲጂታል ማርኬቲንግ እና የብራንዲንግ ድርጅት ከ 5 ዓመት በላይ ለተለያዩ ኩባንያዎች የማስታወቂያ እና የገበያ ጥናት አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል።አሁን ደግሞ የድርጅታችንን የህግ፣ የቢዝነስ ወይም የሂሳብ (Accounting) ስራዎች በቋሚነት የሚሰራልን አማካሪ ድርጅት እንፈልጋለን። ክፍያውን በገንዘብ ሳይሆን እኛ ከምንሰጠው የዲጂታል ማርኬቲንግ አገልግሎት ጋር በቅይይር (Barter) እናከናውናለን። ፍላጎት ያላችሁ inbox አድርጉልን።

            • Groups

              ለዓመታት በንግድ ህግ እና በድርጅት ማቋቋም ስራዎች ላይ የዘለቀ ልምድ ያለው የህግ አማካሪ ድርጅት ነን። አሁን ላይ ለድርጅታችን ዘመናዊ ግራፊክ ዲዛይን እና የቪዲዮ ማስታወቂያ ስራዎችን የሚሰራ ባለሙያ እንፈልጋለን። ክፍያው በገንዘብ ፋንታ ከምንሰጠው የህግ እና የውል ዝግጅት ሙያዊ አገልግሎት ጋር ተመጣጣኝ ተደርጎ በቅየራ ይሰራል። አብሮ መስራት የሚፈልግ ድርጅት በ inbox ወይም በኮመንት ያውራን።

              • Groups

                የእኛ የሂሳብና ኦዲት አማካሪ ድርጅት ለዓመታት ለበርካታ ንግዶች የታክስ እና የሂሳብ ዝግጅት አገልግሎት ሰጥቷል። ለአዲሱ የድርጅታችን ፕሮጀክት የሚሆን ጥራት ያለው የሞባይል አፕሊኬሽን (Mobile App) ማልማት የሚፈልግ የቴክኖሎጂ ድርጅት እንፈልጋለን። ክፍያው በጥሬ ገንዘብ ሳይሆን በሙያችን (በሂሳብ፣ ኦዲት እና የታክስ አማካሪነት አገልግሎት) ምትክ የሚከናወን ይሆናል። የቴክኖሎጂ ድርጅቶች በinbox ወይም በኮመንት አግኙን።

                • Groups

                  የእኔ የህግ አማካሪ ድርጅት ከ 7 አመት በላይ በፍታብሔር ፣ በኢትዮጵያ የታክስና ቢዝነስ ህጎች ላይ ድርጅቶችን ሲያማክር ቆይቷል። ዛሬ ደግሞ አንድ ለየት ላለ offer መጥቻለሁ ጥሩ website የሚሰራ ድርጅት እየፈለኩ ነው ለዛ ድርጅት የምከፍለው ግን በገንዘብ ሳይሆን የእኔን ድርጅት የህግ አገልግሎት ነው በክፍያ መልክ የማቀርበው ። website የሚሰራልኝ ድርጅት አጠቃላይ ዋጋውን ያሳውቀኛል እኔ ደግሞ ከድርጅቱ ለቀረበው ዋጋ ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋና ጊዜ የእኔን አገልግሎት አቀርባለሁ ከዚያም ተደራድረን በሚያስማማን መልኩ አብረን… Read more

                  • Groups

                    12345678910